0
#FastMereja I ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓም በሆስፒታሉ በተካሄደ ስነ ስርዓት ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ለ10 ህጻናት ከክፍያ ነጻ የሆነ የልብ ቀዶ ህክምና ዕድል ሰጥቷል።
ማህበራዊ ኃላፊነቱ በተደጋጋሚ በመወጣት ላይ የሚገኘው ሆስፒታሉ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ሕፃናት እንታደጋቸው በማለት በአመት ለ300 ሕፃናት ነፃ የልብ ህክምና ለመስጠት አቅዶ 67 ያህሉን በገንዘብ ሲሰላ 52 ሚሊዮን ብር ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።
መጪውን 2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአዲስ ዓመት ስጦታ ለ10 ህጻናት ከክፍያ ነጻ የሆነ የልብ ቀዶ ህክምና ሰጥቷቸዋል በገንዘብ ሲተመን 12 ሚሊዮን ብር እንደሚገመት ተነግሯል።
በሆስፒታሉ በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ ሙላቱ ተሾመ፣ የቀድሞው አፈ ጉባኤና የዲቦራ ፋውንዴሽን መሥራች አቶ አባዱላ ገመዳና ሌሎች እንግዶችም ተገኝተው ነበር፡፡
ስራ ከጀመረ ሁለት ዓመት የሆነው ሆስፒታሉ በዋናነት ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቀውን የአዋቂና የሕጻናት የልብና የደረት ቀዶ ህክምና እየሰጠ ይገኛል።
#ማህበራዊ




