#FastMereja – ሁሌም በጎ በማድረግ የሚታወቀው ምህረተአብ ሙሉጌታ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ጳጉሜ 5, 2017 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ከረዩ ሰፈር ለሚገኙ 500 ለሚደርሱ ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ዱቄት እና 5 ሊትር ዘይት ድጋፍ አደረገ።
በዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ወጣቱ ባለጸጋ ምህረተአብ ባስተላለፈው መልእክት “ሁላችን ብንተባበር ካለን ላይ ብናካፍል ብዙ የሚቸግረው ሰው አይኖርም። ሁሉም ሰው አካባቢው ያለ የተቸገረን ሰው በመለየት ቢያግዝ መልካም ነው” ሲል መልእክት አስተላልፏል።
ባለሀብቱ ከህዳሴው ግድብ ምርቃት ጋር ተያይዞ በዝግጅቱ ላይ ደስታውን የገለጸ ሲሆን “ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአለም ሀገራት ቀዳሚዋ ትሆናለች በድህነት የሚያውቋት ኢትዮጵያ ከፍ ትላለች” በማለት ተናግሯል።
የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ባለሀብቱ ለከረዩ ሰፈር ነዋሪዎች ላደረጉት እገዛ አመስግነው ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ድጋፉ የተደረገላቸው ነዋሪዎችም በተደረገላቸው እገዛ መደሰታቸውን ገልፀው ወጣቱ ባለሀብት ምህረተአብ ሙሉጌታንና የተባበሩ አካላትን በሙሉ አመሥግነዋል።
#ማህበራዊ




