banner

እናት ባንክ ለፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ስጦታ አበረከተ

#FastMereja I አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ እናት ባንክ ዛሬ ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም ለፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

እንቁጣጣሽን ከፍቅር የህጻናትና እናቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ያከበሩት እናት ባንክ ከህብረተሰቡ ጋር አብሮ በዓልን በማሳለፍ የመረዳዳትና እሴትን ማጎልበት ዓላማ እንዳደረገ ተገልጿል።

እናት ባንክ ከባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ባንኩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

#ማህበራዊ




Leave a Comment