0
#FastMereja I ሁለገብ ኦንላይን ሶሊሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሁሉ ስፖርት) አገር በቀል የIT ድርጅት ሲሆን ባለፉት አመታት ሁሉ ስፖርት በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ አረጋውያንን እና ህጻናትን በመርዳት ላይ በማተኮር የተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን እየደገፈ የሚገኝ ድርጅት ነዉ።
ሁሉ ስፖርት ጳጉሜን ለበጎ አድራጎት በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከማህበረሰቡ ውስጥ ለተውጣጡ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ለአዲስ አመት መዋያ ከ7,000,000 ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች
መቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ፣ ፍሚናጦስ የአዕምሮ ህሙማን ድርጅት ከአዲግራት፣ ህይወት ብርሀን የህጻናት መርጃ ድርጅት ከመቀሌ፣ ከራይዶን የበጎ አድራጎት ድርጅት ከመቀሌ፣ ጤና አዳም በጎ አድራጎት ከወላይታ ሶዶ፣ ጳጉሜን ለትውልድ ከአርባምንጭ፣ SOS በጎ አድራጎት ከባህርዳር፣ ጣምራ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሀዋሳ፣ ሰውለ ሰው የበጎ አድራጎት ማህበር ከጅማ፣ የኢትዮጵያ የህጻናት ልብ ሕሙማን መርጃ ሲሆኑ በተጨማሪም ክረምቱን ታሳቢ በማድረግ ስፖርታዊ ውድድሮችን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
#ማህበራዊ





1 comment
ከኛ በተሰበሰበ ብር😭