banner

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎችን በምደባ ሊቀበል ነው።

📌 የስያሜ ለውጥ አድርጓል።

#FastMereja I የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረዉን ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለማገዝ በሚያስችል መልኩ ለማደራጀትና የዩንቨርስቲዉን የወደፊት አቅጣጫ ለመወስን ሀገራዊ የጥናት ቡድን ተቋቁሞ የጥናት ዉጤቱ እና የዩንቨርስቲዉ የአዲስ ምዕራፍ ተልዕኮ እና የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ ለሚዲያ መግለጫ ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው ከስያሜው ጀምሮ ለውጥ ያደረገ ሲሆን ሲጠራበት የነበረውን “የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ” በቀጣይ “የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ” በማለት የሚጠራ ይሆናል።

ዩኒቨርሲቲው የህዝብ አገልጋይ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን የታቀደ ሲሆን፣ ከማስተማር ባለፈ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ማገዝ እና ማብቃት እንዲሁም የተቋማት አቅም ግንባታ ላይ ተልዕኮ አድርጎ እንደሚሰራ ተነግሯል።

በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው መስኮች ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም
📍አዳዲስ ተመራቂዎች ወደ አመራር እንዲመጡ አመራር እና አስተዳደር ላይ መስራት።
📍ሀገሪቱ የምትመራበትን እቅድ መደገፍ እና አዳዲስ ማመንጨት።
📍ፋይናንስ እና ኢኮኖሚስቶችን በብዛት ማሰልጠን።
📍በህግ ላይ በትኩረት መስራት።
📍በፐብሊክ ሴክተሩ ላይ በዲጅታል እና ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው የፈጠራ እና የአስተዳደር ማዕከል ማደራጀቱንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ መዳረሻው የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን እንደሆነ ተነግሯል።

ዩኒቨርሲቲው ከፐብሊክ ሴክተሩ በተጨማሪ ከ12 ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ የተነገረ ሲሆን ተማሪዎችን ምደባ ከታወቀ በኋላ ጥሪ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት 30 ዓመታት የሀገራችንን ፐብሊክ ሴክተር በትምህርት፤ በምርምር፤ በስልጠና እና በማማከር ዘርፎች በመደገፍ ሴክተሩ ለሀገር ግንባታ የበኩሉን እንዲወጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደቆየ ተገልጿል።





Leave a Comment