banner

5ኛው የአርኪ የሪል እስቴቶች የቤትና የሱቅ ሽያጭ ኤክስፖ

#FastMereja I አርኪ የሪል እስቴቶች የቤትና የሱቅ ሽያጭ ኤክስፖ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ከጥቅምት 14-16/2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።

አርኪ ሆም ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል እና በሚሊንየም አዳራሽ ባዘጋጃቸው አራት ተከታታይ ኤክስፖዎቹ ከሃያ አምስት ሺ በላይ ሰዎች የጎበኙት እንዲሁም ከስምንት መቶ ያላነሱ ሰዎች ቤት የገዙበት ትልቅ የቤት ፈላጊና የቤት አልሚዎች የሚገናኙበት ኤክስፖ ነው፡፡

የዘንድሮ ለየት የሚያደርገው ሁሉም የሪል እስቴት አልሚዎች ታላቅ ቅናሽ የሚያደርጉበት ከመሆኑ በተጨማሪም በዚህ ኤክስፖ ቤትና ሱቅ የሚገዙ የቤት እቃ በነፃ የሚሸለሙበት እድል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ለተከታታይ ሶስት አመታት አራት ትልልቅ የሪል እስቴት የቤትና ሱቅ ሽያጭ ኤክስፖዎችን ያዘጋጀና በሃገራችን ለመጀመርያ ጊዜ የተዘጋጀውን ኢትዮ ሪል እስቴት አዋርድ 2017 አዘጋጅ ነው፡፡

#ኹነት




Leave a Comment