banner

የኢትዮጵያ ዲጄዎች ድምጻዊያን ከእኛ ይልቅ ቲክቶከሮችን እያስቀደሙ ነው አሉ።

#FastMereja I የኢትዮጵያ ዲጄዎች ማህበር ድሮ ድሮ አንድ አርቲስት አልበም ሊያወጣ ሲል ዲጄውን ይሰበስብና ግማሽ ሊትር ውሀ ጋብዞ አልበሜን ስሙልኝ ብሎ ይጎዘጎዛል ከዛ የሙዚቃ ባለሙያ ስለሆንን በትክክል ሰምተን ጥሩ የሆነውን በየክለቡ እና በየዝግጅቱ አጫውተን እናስለምድለታለን።

አልበሙ ፌመስ ከሆነ በኋላ ለማህበራቸ‍ን የአመሰግናለሁ ደብዳቤ እንኳን አይልኩም የጋራ ጥቅም ስለሆነ ይመቸው ብለን እንዘለዋለን።

አሁን ደግሞ የሙዚቃን አልበም ሚገመግሙት ቲክቶከሮች ሆነዋል ምንም አይነት ዲጄ ተጠርቶ እንደሙያ ስማልኝ ቀርቷል። በዚህ አንድ አመት ውስጥ የወጡ ትልልቅ የአልበም ሊስኒንግ ፓርቲዎችን ብታዩ ዲጄው አይጠራም ግን በየክለቡና በየዝግጅቱ እረ ዘፈኔን አጫውቱልኝ ይባላል።

ኢትዮጲያ ውስጥ ከ7000 በላይ ዲጄ አሉ ሁሉም ዲጄ የኢትዮጲያን ሙዚቃ ለኢትዮጲያውያን አሽሞንሙኖ ቆንጆውን ከተመታው አቻችሎ በማቅረብና በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም ነን። ወደፊትም ይቀጥላል።

እና ስንጠቀልለው ለምን አልተጠራንም እያልን ሳይሆን አሁንም ሙያው የተሳሰረ መሆኑን አትርሱት ዞሮ ዞሮ እዚሁ ናችሁ ለማለት ያህል ነው ብለዋል።

10 comments

Hanicho Ye Nobele October 30, 2025 - 7:27 am

ምስኪን ዲጄዎች ሰልፍ ለምን አትወጡም ታድያ 😉

Reply
PM Mikiyas Solomon October 30, 2025 - 7:28 am

Market share ሚባል ነገር አለ የት ነበሩ በፊት እንዴ?😁

Reply
Mekedes Fekadu October 30, 2025 - 7:28 am

የስፖርቱን ቋጨን ስንል ደሞ ወደ ዲጄዎች አይ መከራችን

Reply
ጉን ዳን October 30, 2025 - 7:31 am

የድሮ ስርዐት ናፋቂ

Reply
Ghion Ethiopia October 30, 2025 - 7:32 am

ጊዜው የቲክቶከር ነው 🙂።

Reply
Abrham Ch October 30, 2025 - 7:32 am

ወቅቱ የቲክቶከር ነው እናተ አሁንም ሲዲ ላይ ናቹ

Reply
Yonas Yo-nas October 30, 2025 - 7:33 am

ጋዜጠኛ vs tiktoker
Dj vs tiktoker ሞቅ ሞቅ አርጉት እንጂ

Reply
Mule Terefe October 30, 2025 - 7:34 am

Update ur self time is changing bro

Reply
Mubi Gunners October 30, 2025 - 7:38 am

ይሄ አሪፍ ፉክክር ይኖረዋል አደራ ዲጄዎች ጠንከር በሉ 👈

Reply
Ab As October 30, 2025 - 7:40 am

በነገራችን ላይ ቲክቶክ የብዙ ባሙያዎችን እንጀራ ሰብስቦ ከበላ ቆዬ ማሳያ ጋዜጠኞች አሁን ላይ ማንም አይሰማቸውም የፊልም ተዋናዮች በሁሉም ዘርፍ ያሉ በኮሜዲም ጨምሮ አሁን ደሞ በሙዚቃ እየሰማን ነው ነገሮች ተቀይረዋል ጊዜውን ቲክቶከሮች ናቸው ያጨናነቁት ይገርማል ድሮ ብራንድ ለመሆን የፊልም ተዋናይ ነበር አሁን ቲክቶከር ናቸው ማስታወቂያም እንዲሁ ይገርማል ብቻ

Reply

Leave a Comment