banner

ፎሊክ አሲድን ከእርግዝና በፊት በመውሰድ የአከርካሪ አጥንት እና ሌሎች የነርቭ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮችን መከላከል ይገባል ተባ

ፎሊክ አሲድን ከእርግዝና በፊት በመውሰድ የአከርካሪ አጥንት እና ሌሎች የነርቭ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮችን መከላከል ይገባል ተባለ

#FastMereja I “አክስለሬት አክሽን ፎር ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ” በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ቀንን አስመልክቶ ሪች አናዘር ፋውንዴሽን፣ ከሮተሪ ሴንትራል መላ ክለብ፣ ከአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጋላጭነታቸው ሰፊ የሆኑ እናቶችን ለይቶ ቀጣይ እርግዝናቸው የታቀደ በማድረግ ፎሊክ አሲድ መድሃኒትን ከእርግዝና በፊት እንዲያገኙ ተደራሽነቱን በማስፋት እና በማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎችን ለመዳሰስ እንዲሁም በመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና ቀጣይነት ያለቸው ጅማሮችን ለማሳደግ ያለመ ፕሮግራም በጊዮን ሆቴል ተካሂዷል።

ይህ ዝግጅት የተለያዩ ከችግሩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ንቅናቄው ከተለያዩ የህክምና ተቋማት ከተውጣጡ በእናቶች እና ህፃናት ጤና ዙሪያ እያገለገሉ የሚገኙ 80 ባለሙያዎችን የሁለት ቀን የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት የተጀመረ ሲሆን በዛሬውም እለት የሚዲያ አካላት አጋር ድርጅቶች እንዲሁም በችግሩ የተጠቁ ህፃናትና ወላጆቻቸው በተገኙበት ለባለሙያዎቹ የሰርትፍኬት አሰጣጥ ስነስርአት ተካሂዷል::

ስፓይና ቢፊዳ የአከርካሪ አጥንት እና የነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር ሲሆን የአካል እና የአእምሮ እድገት ውስንነቶችን ጨምሮ የዕድሜ ልክ አካል ጉዳተኝነትን ሊያስከትል ይችላል። በሽታው በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን በየዓመቱ የሚጎዳ ሲሆን ቅድመ መከላከል ለነገ የማይተው አስፈላጊ ስራ ነው::

ፎሊክ አሲድን በእንክብል መልክ ከእርግዝና በፊት መውሰድ የአከርካሪ አጥንት እና ሌሎች የነርቭ ዘንግ እንዲሁም ተያያዣነት ያላቸውን የአፈጣጠር ችግሮችን ለመቀነስ የተረጋገጠ ሳይንሳዊ መፍትሄ ሲሆን በርካታ ሃገራት ይህንን በመተግበር የአፈጣጠር ችግሮችን በእጅጉ ቀንሰዋል።

#ጤና





1 comment

ፍቅር ወይስ በቀል October 30, 2025 - 9:40 am

የመድሃኒቱን ጨጓራ ይጎዳል የሚባለው ምን ያህል እውነት ነው? የሚያውቅ ያስረዳኝ plisss

Reply

Leave a Comment