#FastMereja | በእንሰሳት ሃብት ልማት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ትኩረት ያደረገው በኢትዮጵያ ቀዳሚው የእንስሳት ዘርፍ አውደ-ርዕይ እና ጉባኤ ከዛሬ ጥቅምት 20-22 ድረስ በሚሊኒየም አዳራሽ ለተሳታፊዎች እና ጎብኚዎች ክፍት ሆኗል።
14ኛው የኢትዮ ፖልተሪ ኤክስፖ 10ኛው የአፍሪካ እንስሳት ዓውደ-ርዕይና ጉባዔ እንዲሁም 5ኛው የአፒካልቸር እና አኳካልቸር ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርዒትና ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው የባዮ ኢነርጂ የንግድ ትርዒት ጥራት ያላቸውን የዘርፉ ዋነኛ አንቀሳቃሾች በተገኙበት ነዉ የተጀመረዉ።
በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የንግድ ትርዒቶች አዘጋጅ በሆነዉ በፕራና ኢቨንትስ ተዘጋጅቶ ለ3ቀናት የሚቆየዉ አዉደ-ርዕይ ላይ ከ5000 በላይ የንግድ ጎብኚዎች ተሳታፊ ናቸው።
ከዚህ በፊት በነበሩት መርሀ-ግብሮች ዓውደ-ርዕዩ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ በዘርፉ ተዋንያን መካከል ለመቀራረብ ምቹ መድረክ በመሆን፣ ልምድና ተሞክሮ ለመጋራት በማስቻል የአቻ ለአቻ የንግድ ትስስር መርሀ-ግብሮችን በማዘጋጀት የላቀ ሚና ተጫውቷል።
በዘንድሮዉ ዓዉደ-ርዕይ ላይ ከ14 ሃገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ ዓለም ዓቀፍ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች ፣የግብርና ሚንስትር ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ የሀገራት አምባሳደሮች ፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የንግድ ጎብኚዎች በመክፈቻው ላይ ተሳትፏል።
#ኹነት




