banner

በአዲስ አበባ ከ11 ሺህ በላይ እግረኞች ተቀጡ፣ በተለይ ኤርፎን አድርጋችሁ የምትጓዙ ተጠንቀቁ

#FastMereja I በአዲስ አበባ የመንገድ ትራንስፖርት ለመቆጣጠር የወጣዉን ደንብ በ3 ወራት 11 ሺህ 508 እግረኞች መቀጣታቸው ተገለጸ።

እነዚህ እግረኞች ትክክለኛ የመንገድ አጠቃቀም ያልተከተሉ ሆነዉ በመገኘታቸዉ 6,108 የሚሆኑት በገንዘብ እንዲቀጡ ተደርጓል።

እንዲሁም 5499 እግረኞች ደግሞ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ተቀጥተዋል ተብሏል።

ኤርፎን አድርገዉ መንገድ በማቋረጥ እንዲሁም ለእግረኞች ተብለዉ የተተከሉ አጥሮችን የዘለሉ እግረኞች በቅጣቱ እንደምክንያት መቀመጡን ተገልፆል።

የእግረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዝ ይዘዉ የተጓዙ ÷ በትክክለኛ የእግረኛ መሻገሪያ መንገድ ያላቋረጡ እንዲሁም ደግሞ በተሽከርካሪ መንገድ ያለ በቂ ምክንያት በቆሙ እግረኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ በተጨማሪም ከ100 እስከ 150 ብር እንዲቀጡ መደረጉ ተሰምቷል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ነው የዘገበው።

3 comments

ጥበብ ከጲላ ጦስ October 30, 2025 - 12:56 pm

መንግስት የዉጭ ብድርን ለመክፈል ከብዶታል ገና ከዚህ የበለጠ ነገር ያመጣል::

Reply
Bahredin Seid October 30, 2025 - 12:58 pm

የሰው እግር የማይስማማውን ኮሊደር ለምን ረገጡ እሰይ🤣🤣

Reply
Sebli Ňã October 30, 2025 - 12:58 pm

ባለመኪናውን አስጨልለው ደሞ ወደኛ ዞሩ🤔

Reply

Leave a Comment