banner

ኮድ 4 ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግ እየጣሱ አስቸግረውኛል ሲል ትራፊክ ማኔጅመንት አስተወቀ

#FastMereja I በአዲስ አበባ የመንግስት ወይም 4 ቁጥር የለጠፉ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግ እየተላለፉ አስቸግረውኛል ሲል የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ተናገረ፡፡

በሶስት ወር ውስጥም ከ270 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪ ሾፌሮች መቀጣታቸውም ሰምተናል፡፡

ኮድ 4 መኪና አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግን በመጣስ፣ እንደፈለግን እንሁን ማለታቸው ትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር ስራውን በሚያከናወንበት ጊዜ እንቅፋት እንደሆኑበት ቢሮው አስረድቷል።

በአዲስ አበባ ትራፊክ ማነጅመንት የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው ኢቴሳ ህግን ለማስከበር መነሻው ህግ ነው፣ በህግ ፊት ደግሞ ሁሉም እኩል ነው ቢባልም አንዳንድ ባለስልጣናት ግን እንደፈለጉ ባልተፈቀደ መንገድ ያሽከረክራሉ፣ በተቃራኒ መንገድ ይነዳሉ ብለዋል፡፡

ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተሰመረ መስመር ጭምር ማሽከርከር ይመርጣሉ ይህ ድርጊታቸው ደግሞ ለትራፊክ አደጋ መከሰት ጭምር ምክንያት እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ህግን ፣የትራፊክ መብራትን በሚጥሱና ባልተፈቀደ መንገድ የሚያሽከረክሩ በለስልጣናትንም ሆነ ማንኛውንም አሽከርካሪ የሚቻለውን እየቀጣን ፣ ጥሶ የሄደውን ታርጋ ቁጥሩን መዝግቦ በመያዝ በሚመለከተው አካል በማስጠራት ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ይደረጋል ሲሉ አቶ አያሌው ኢቴሳ ነግረውናል፡ ሲል ሸገር ሬዲዮ ነው የዘገበው።

10 comments

ፍቅር ያሸንፋል October 30, 2025 - 6:19 pm

ለጌታም ጌታ አለው😂

Reply
Ebenezer K Zeleke October 30, 2025 - 6:19 pm

ሠማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ 😌

Reply
Iyobi Dumalo October 30, 2025 - 6:21 pm

ያስፈራራሉ በስሜ 4 ቁጥር በጥቁር ቀለም አንድ ወር ብቻ ነው ነው የሚቀራቸው
ለአዲሱ ታርጋ

Reply
Dariye Hayiso October 30, 2025 - 6:22 pm

በክልል ከተሞች ለቁጥጥር እንኳን ለመቆመ ፈቃደኛ አይሆኑም።
ለምን ታስቆመናለህ በማለት ይዝታሉ😢

Reply
Fetu Shifa Siraj October 30, 2025 - 6:22 pm

የኢቴሳ ልጅ ነገ ደብዳቤ በእጁ ይገባል

Reply
ጉን ዳን October 30, 2025 - 6:22 pm

ሕጉ ራሱ ሕጉን አያከብርም

Reply
Iyobi Dumalo October 30, 2025 - 6:22 pm

4 ቁጥር ስለያዙ ብቻ ራሳቸውን እንዴ ጠቅላይ ሚኒስትር ያያሉ

Reply
ቦሮበር ከነጋሾ October 30, 2025 - 6:23 pm

እንዴ ህግኣለንዴ

Reply
Teyo Desalegne October 30, 2025 - 6:23 pm

በተለይ በተለይ ከሲኤምሲ ወደ መገናኛ የሚሄዱ ኮድ4 መኪኖች ያሳዝናል

Reply
አማሪያ ከጅጅጋ October 30, 2025 - 6:24 pm

“ድሮ የሀጎስን ዛሬ የጫላን መኪና ማስቆም አይቻልም”
እንዲህ ማድረግ ካልቻሉ ምኑን ተሾሙት😂😂😂😂

Reply

Leave a Comment