#FastMereja I በሃገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ “ቶሎ” በሚል ስያሜ የተገጣጠመዉን የኢንዳክሽን ምድጃ አምራች የሆነው ግሪን ሲን ኢነርጂ የመጀመሪያዉን የኢንዳክሽን ስቶቭ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ተቋም በዛሬዉ እለት ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ስራ አስጀምሯል።
በዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚደገፈው በኢትዮጵያ የንፁህ ምግብ ማብሰል ዘርፍ ቁልፍ ሚና ያለው ግሪን ሲን ኢነርጂ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኢንዳክሽን ስቶቭ መገጣጠሚያ እና የማምረቻ ፋሲሊቲ ነዉ በዛሬዉ እለት ስራ ያስጀመረዉ።
ዛሬ ይፋ የተደረገዉ ቶሎ ኢንዳክሽን ምድጃ 9ዐ% ኃይል ቆጣቢ ፈጣን ሙቀት ከትክክለኛ የሙቀት መቆጣጠሪያ ጋር ማንኛውንም ቦታ ከፍ አድርጎ ማስቀመጥ የሚያስችል የሚያምር፣ በዘመናዊ ዲዛይን የተሰራ የቴክኖሎጂ ዉጤት ነዉ ተብሏል።
ይህ ቴክኖሎጂ በዓመት 63,000 ለሚገመቱ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የቤት ውስጥ የአየር ብክለትን በመቀነሱ ሴቶችን ከ500 ሰአታት በላይ በመቆጠብ ማገዶን በመሰብሰብ ፣የደን መጨፍጨፍን በመዋጋት የቤትን ደህንነት በማጎልበት እና የአረንጓዴ ልማትን በማስቀጠል እና የከተማ ልማት ፕሮግራሞችን በመደገፍ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዉ የስቶቮቹ ዋጋም ከኢትዮጵያ 6000 ብር ጀምሮ ማግኘት እንደሚቻል የግሪን ሴን መስራች ወ/ሮ ረቂቅ በቀለ ገልፀዋል።
ግሪን ሲን ኢነርጂ የኢንዳክሽን ምድጃዎችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠምና በማምረት ለብዙዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ ጥገኝነቶችን በመቀነስ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት አጀንዳ በማሳደግ ላይ ያለ ትልቅ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።
የግሪን ሲን ኢነርጂ ኢንዳክሽን ምድጃ መፍትሄዎች የተነደፉት በፀሃይ ሃይል የሚሰሩ ራቅ ያሉ ቦታዎችን እና ከፍተኛ አቅም ያለው የማብሰያ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት ነዉ።





1 comment
የሃገር ዉሥጥ ሲሆን ሥሙም አያምርም