banner

አናንያ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል እና ጽጌረዳ የውስጥ ደዌ ህክምና ማዕከል ተዋሃዱ

#FastMereja I የቀድሞ አናንያ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል እና ጽጌረዳ የውስጥ ደዌ ህክምና ማዕከል መዋህዳቸውን አስታወቁ።

ሁለቱ የህክምና ማዕከላት ለበርካታ አመታት ሁለቱም ለበርካታ ሰዎች ህክምና ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት “ጽጌሬዳ አናንያ የእናቶችና ህፃናት የውስጥ ደዌ እና ቀዶ ህክምና ማዕከል” በሚል ስያሜ አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ተገልጿል።

የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አበበ ደምስስ እንደገለጹት የሁለቱ ተቋማት ውህደት በሕክምና ማዕከላቱ በተናጠል ይሰጡ የነበሩ የህክምና አገልግሎቶችን በተደራጀ እና በብቁ ባለሞያዎች ለመስጠት እንዲሁም ዘመን ያፈራቸውን የህክምና ማሽኖች አሟልተን አገልግሎት እንድንሰጥ አድርጎናል ብሏል።

ጽጌሬዳ አናንያ የሕክምና ማዕከል አገልግሎቱን እየሰጠ ያለው ለህክምና አገልግሎት ተብሎ በተገነባው ዘመናዊ እና ሁለገብ ህንፃ ላይ ሲሆን ህንፃው የልዩ ፍላጎት ታካሚዎችን ያስቀደመ ፣ የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የደረጀ ፣ ቴክኖሎጂው በደረሰባቸው የህክምና መሳሪያዎች የተደራጀ ማዕከል እንደሆነ ተገልጿል።

አናንያ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል የ25 አመት እና ጽጌረዳ የውስጥ ደዌ ህክምና ማዕከል ለ15 አመታት በዘርፉ ላይ የቆዩ የህክምና ማዕከላት ናቸው።





Leave a Comment