banner

በእርግዝና ወቅት ፎሊክ አሲድን አለመዉሰድ ህፃናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር እንዲወለዱ ምክንያት መሆኑ ተገለፀ

#FastMereja I ዓለም አቀፍ “የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ዉስጥ ከመጠን በላይ ፈሳሽ ክምችት ” ወርን በሆፕ ኤስ ቢ ኤች ግብረሰናይ ድርጅት አዘጋጅነት ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም በዛሬዉ እለት አካሂዷል።

በዛሬዉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ ስለ ነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ችግር እና የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት ወይም “የስፖይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ” በሽታ ምንነት እንዲሁም የበሽታውን መንስዔ እና መፍትሔ በባለሙያዎች የታገዘ ግንዛቤን ማስጨበጫ መርሀ ግብር ነዉ የተካሄደዉ።

ስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ) ችግሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር በአግባቡ አለመዘጋት/ክፍተት ነው።

ሃይድሮሴፋለስ (የጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት) ሲሆን ይህም የአዕምሮ ግፊት እንዲጨምርና የራስ ቅል ላይ መሰንጠቅን ሊያስከትል ይችላል።

በሀገራችን በየዓመቱ ከ30,000-50,000 በላይ የሚሆኑ ህጻናት ከዚህ በሽታ ጋር እንደሚወለዱ በዚህም ምክንያት እነዚህ ሕጻናት ለዕድሜ ልክ የአካል ጉዳት ብሎም ለሞት ተጋላጭ እንደሆኑም ተገልጿል።

ነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ችግር እና የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ ከመጠን በላይ ክምችት ችግር በተመለከተ ችግሩ ያለባቸው ህፃናት ትኩረት እንዲያገኙ እና በችግሩ የተጠቁ ህፃናት እና ቤተሰቦች ተገቢውን እንክብካቤ እና ትኩረት እንዲሰጣቸው በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን እሳቤ ለመቀየር የተዘገጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ነዉ።

ሆኘ ኤስ.ቢ.ኤች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ በጎ አድራጎት ማህበራት ኤጀንሲ ፈቃድ ተሰቶት የነርቭ ዘጓግ ክፍተትና የጭንቅሳት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት ያለባቸው ህጻናት ላይ የሚሰራ የመጀመርያው ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ነው።

የድርጅቱ ዋና አላማ ችግሩ በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ የኢትዮጲያ ህጻናት ተጠቂ እያደረገ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት አንዲያገኝ ማድረግ እንዲሁም በችግሩ የተጠቁ ህጻናት እና ቤተሰቦች ህክምና እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።





Leave a Comment