0
#FastMereja I የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች “የኢትዮጵያ ወጣቶች የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ማህበር” የተሰኘ ህጋዊ ዕውቅና ያለው ማህበር መሰረቱ።
ማህበሩ የአባላቱ ሙያዊ ክብር ከማስጠበቅ ባሻገር ማህበራዊ ሚድያን ዝቅ አድርጎ የማየት አስተሳሰብን እንዲቀረፍ ይተጋል ተብሏል።
አባላቱ ለዘገባ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ክልከላና እገዳ እንዳይደረግባቸው መታወቂያ የመስጠት፣ አባላቱ ገቢያቸውን ከፍ ለማድረግ ጥረትና በተለይም የማርኬቲንግ ስልት በመንደፍ መንቀሣቀስ፣ በአባላቶች ላይ ጉዳትና አላስፈላጊ ተፅዕኖ ሲፈጠር በጋራ የመቆምና የመከላከል ተግባር የማህበሩ ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው ተብሏል።
አባላቶች ከዓለም አቀፋዊም ሆነ አህጉራዊ የሶሻል ሚዲያ ህብረሰብ ጋር በመገናኘት የልምድ ልውውጥ ፤ ስልጠና እንዲሁም ጉባኤዎችና ዝግጅቶች ላይ ለመሣተፍ ወይም ለመዘገብ ከሀገር ውጪ ለመውጣት ሲፈልጉ ለጉዞአቸው የሚያስፈልጉ የዶክመንት ጉዳዮችን ማመቻቸት ስራዎችን ይሰራል።
ከ5ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የማህበሩ አባል መሆን እንደሚችል ተገልጿል።





7 comments
Mahiber mebzatu aydel wanaw chgirachn
Esky ye wutet mahber yhun koyito saykasesu
አንድም የማውቀው ሰው አላየሁም።
ፐ በጣም አሳሳቢው ጉዳይ መፍትሔ ተገኘለት 😑😑
👍
Melat Nigussie የኛ አብሪ ኮኮብ🙌❤
እንዴ እኔስ በብሄሬ ምክንያት ነው ያልተጠራሁት?💀
Uuuuu