banner

“መንታ ገጽ” መጽሐፍ ተመረቀ።

#FastMereja I በካሳሁን ተረፈ የተጻፈው “መንታ ገጽ” መጽሐፍ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋልያ መጽሐፍ አዳራሽ ተመረቀ።

መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ደራሲና ሐያሲ አያልነህ ሙላት፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል እና ሌሎች ታዳሚያን በተገኙበት ተመርቋል።

ካሳሁን በአሁኑ ሰዓት ለአንባቢያን ካቀረበው “መንታ ገፅ” የአጫጭር ልብወለድ መፅሐፉ አስቀድሞ ሀገር አበ … ቃላት፣ ምኑን ተለወጠ እና የጤዛ ፈገግታ
የተሰኙ የግጥም መፅሐፎችን ለአንባቢያን አድርሷል

እንዲሁም ታትመው ለአንባቢያን ከቀረቡ ስራዎቹ ባሻገር በሻሸመኔ ፋና ሬዲዮ በዘመነ ሀልዮ ፕሮግራም ላይ ለበርካታ ወራት በተከታታ የቀረበ “ዳምጠው አባ ዝናብ” ተራኪ ግጥም እንዲሁም በአሰላ FM የተላለፈ “ደራሽ ” ተከታታይ የሬዲዮ ድራማውን ጨምሮ ያልታተሙ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ አዝናኝ እና አስተማሪ በርካታ ተራኪ ግጥሞች ለተደራሲያን አበረክቷል ።

ካሳሁን ከግጥሞች፣ ከተራኪ ግጥሞች እና ከአጫር ልቦለዶቹ ባሻገር ነፋስ ጋላቢዎች፣ ፍቅር በሞት ሚዛን፣ ወጥመድ፣ የተምታቱ ቁልፎች፣ የበደል አዙሪት፣ የፍቅር አዳኞቹ፣ ፍርሀት። የባቢሎን ፅዋ እና ሌሎችም በርከት ያሉ የሙሉ ጊዜ ድራማዎች እና ተዘጋጅተው ለተመልካች ያልቀረቡ “ጥልፍልፍ” እና “በሰው ላይ” የተሰኙ የፊልም ድርሰቶችን ፅፏል ።

ካሁን ተረፈ የተወለደው በሻሸመኔ ከተማ ነው።





Leave a Comment