banner

ለኢትዮጵያ ኩባንያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ማሻሻል ያለመ መድረከ ተካሄደ

#FastMereja I ኢትዮጵያዊ ኩባንያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሻሻል የተዘጋጀ ከፍተኛ ደረጃ የንግድ እና የፋይናንስ መድረክ ዛሬ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሄደ።

መድረኩ የኩባንያዎች አቅምን ከፋይናንስ መፍትሄዎች ጋር በተግባር ለማገናኘት የተዋቀረ የመግባባት እና የእርምጃ መድረከ ነው ተብሏል።

የፋይናንስ ተደራሽነት የኩባንያ ብቻ ጉዳይ አይደለም የተባለ ሲሆን የአገር ምርታማነትን እና ተወዳዳሪነትን የሚያነሳ ቁልፍ ነጥብ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል። ተገቢ የሰራ ካፒታል እና የኢንቨስትመንት ፋይናንስ ሲኖር ኢትዮጵያ በሥራ ፈጠራ፣ በምርታማነት እድገት፣ በዋጋ ሰንሰለት ጥራት እና በውጭ ገቢ የሚታዩ ተግባራዊ ውጤቶችን ታገኛለች ተብሏል።

መድረኩ 250 የተመዘገቡ ተሳታፊዎችን ያካተተ ሲሆን ከእነሱም 170 ኩባንያዎች፣ ወደ 25 የሚጠጉ ባንኮች/የፋይናንስ ተቋማት፣ ኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ኢንቨስትመንት አማካሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የመንግስት ተወካዮች ተገኝቷል።

መድረኩ በGIZ Ethiopia እና KfW Development Bank የተመራ ሲሆን በEAP Consulting እና Galani Roastery & Cafe ጋር በትብብር ተካሂዷል።





Leave a Comment