banner

በስህተት ወደ ባንክ አካውንታቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር ለባለቤቱ መለሱ፡፡

#FastMereja I የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር በታማኝነት ለባለቤቱ መልሰዋል፡፡

ህዳር 13 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከአዋሽ ባንክ አቶ አብዱል ሰመድ መሃመድ የተባሉ ደንበኛ ወደ አሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለአቶ መሃመድ ኢብራሂም 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር እንዲላክላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ገንዘቡ በስህተት ወደ አቶ ቻላቸው ጌጡ አካውንት ገቢ ሆኗል፡፡

አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን ገንዘብ በታማኝነት ለባለቤቱ ተመላሽ በማድረግ አርዓያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ላሳዩት ታማኝነት እና አርዓያነት ያለው ተግባር አቶ ቻላቸው ጌጡን አመስግኗል።

3 comments

Tamrat Tesfaye December 9, 2025 - 2:31 pm

ምን ይባላል እሺ ይሄ

Reply
ፍቅር ያሸንፋል December 9, 2025 - 2:32 pm

እናቱ ስትመርቀው አሜን ሳይል የቀረ ሰው😭

Reply
Ebsa Gutema December 9, 2025 - 2:32 pm

የኔ እድል እንደ ቁ*ዬ የተዘቀዘቀ ነው😥 ምን አለ ለኔ ባረገው መመለሱን ፈጣሪ ነበር ሚያቀው

Reply

Leave a Comment