0
#FastMereja : ዛሬ በመዲናዋ እምብርት በሚገኘው ታሪካዊው የመስቀል አደባባይ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው “የአእላፋት ዝማሬ” በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል። ይህ መርሐ-ግብር ከዝማሬው ባለፈ የቤተክርስቲያኒቱን አንድነትና መንፈሳዊ ጥንካሬ ለዓለም የሚያሳይ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን በአንድ ዓይነት ልብስና ድምፅ በመታጀብ፣ ጥንታዊና ዘመናዊ ያሬዳዊ መዝሙራትን ያቀርባሉ።
ከሁሉም የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት የተሰባሰቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን አደባባዩን በነጭ ልብስ እንደሚያስውቡት ይጠበቃል።
ዝግጅቱ በተለያዩ በበርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ለዓለም አቀፍ ምዕመናን በቀጥታ ይተላለፋል።

4 comments
ወንዶች መምጣት አይችሉም?
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ለዘላለም ትኑር ፈተና ቢበዛባትም ማንም ቢሰድባትም ማንም ቢያሳድዳትም እንደገና ታብባለች እንደ እኔ የመንፈስ ቅናት ያለበት ማነዉ?
እኔ አሁን ልሂድ ልቅር እያልኩ ገና እያሰብኩ ነው
እንዴት እንደምወደው