0
#FastMereja I በዛሬው ዕለት ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የሚያደርጋቸው በረራዎች መሰረዛቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
አየር መንገዱ ለመንገደኞች በላከው አጭር የጽሁፍ መልዕክት በረራዎቹ የተሰረዙት “ከዕቅድ ውጪ በሆነ ምክንያት” መሆኑን የገለጸ ቢሆንም፣ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።
የትግራይ ክልል ትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ታደለ መንግሥቱ በረራዎች መቋረጣቸውን አረጋግጠው፣ ዝርዝር ምክንያቱን ግን እንደማያውቁ ገልጸዋል።
አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአየር መንገዱ ኃላፊ በረራዎቹ ለዛሬ ብቻ መሰረዛቸውን ጠቅሰው፣ የቀጣይ ቀናት ሁኔታ በሚኖረው ተጨባጭ ሁኔታ እንደሚወሰን አስታውቀዋል።
መንገደኞች ወደ አየር መንገዱ ወይም ወደ የጉዞ ወኪሎቻቸው በመደወል ተጨማሪ መረጃ እንዲያገኙ ተመክሯል።
