banner

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ6,194 መምህራንን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በይፋ አስጀመሩ

​
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ለዓመታት ሲያነሱት ለቆዩት የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ታሪካዊ ምላሽ በመስጠት፣ የማኅበር ቤቶች ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
​
​ተጠቃሚዎች፦ በ57 ማኅበራት የተደራጁ 6,194 መምህራን።
​የመሬት ስፋት፦ በከተማዋ የተለያዩ ሳይቶች የሚገኝ 40 ሄክታር መሬት።
​የመንግስት ድጋፍ፦ 24 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ መሬት በነፃ የቀረበ ሲሆን፣ አስተዳደሩ 5 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ፈጽሟል።
​የመምህራን ድርሻ፦ የግንባታውን ዋጋ 25 በመቶ አስቀድመው የቆጠቡ።

​ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ ይህ ፕሮጀክት አስተዳደሩ ለመምህራን ያለውን ከፍተኛ ክብር በተግባር የገለጸበት ነው። “መምህራን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ መሆናቸው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩና በትኩረት ትውልድ የማነጽ ሥራቸውን እንዲወጡ ያግዛቸዋል” ብለዋል።

​ከንቲባዋ አክለውም፣ ይህ ዕድል ከመምህራን በተጨማሪ ለጤና ባለሙያዎችና ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞችም በተመሳሳይ መልኩ ተደራጅተው ለሚጠባበቁ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

​የዕጣው ተጠቃሚ የሆኑ መምህራን በበኩላቸው፣ ላለፉት ዓመታት የነበረባቸው የመኖሪያ ቤት ችግር በዚህ መልክ መፈታቱ ለሥራቸው ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥርላቸው በደስታ ገልጸዋል።

Leave a Comment