banner

ሚድሮክ በሻኪሶ ከተማ የአውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ

#FastMereja I ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ የሚያስገነባው አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

​በታላቁ የምረቃና የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተገኝተው የመሠረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

​ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በመስከረም 2019 ዓ.ም ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ታውቋል። የአየር ማረፊያው መገንባት ለሻኪሶ ከተማ ዕድገት መፋጠንና ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

​በመርሐ ግብሩ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት፣ አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች ተገኝተው ለልማት ሥራው ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ይህንን ግንባታ በማስጀመሩ “የአካባቢውን ማህበረሰብ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል” ብሏል።

Leave a Comment