#FastMereja I በሲንጋፖር አንድ የ97 ዓመት አዛውንት ከልጃቸው ጋር የነበራቸውን የህግ ክርክር በማሸነፍ ለ50 ዓመታት አብረዋቸው የቆዩትን ፍቅረኛቸውን የማግባት መብት አግኝተዋል።
የ97 ዓመቱ አዛውንት (በስም ያልተጠቀሱ) ከፍቅረኛቸው ጋር ለመጋባት ሲወስኑ፣ ሁለተኛ ልጃቸው “አባቴ የመወሰን አቅም የላቸውም” በሚል ክስ መስርቶባቸው ነበር።
ልጁ አባቱ በ2017 ዓ.ም ከወደቁ በኋላ የመርሳት በሽታ እንደያዛቸውና በሴቲቱ እየተመሩ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ ነበር።
አዛውንቱ በበኩላቸው ልጃቸውንና የልጅ ልጃቸውን ከውርስ ውጭ በማድረግ፣ 3.8 ሚሊዮን የሲንጋፖር ዶላር እና የኩባንያ ንብረቶች እንዲመለሱላቸው የመልስ ክስ መስርተዋል።
የህክምና ማስረጃዎች አዛውንቱ እድሜያቸው ቢገፋም፣ ስለ ትዳርና ንብረት የመወሰን ሙሉ ብቃት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
ዳኛ ሾባ ናይር እንደገለጹት፣ ልጁ አባቱ አቅም የላቸውም ቢልም በ2019 ዓ.ም አባቱ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲቀጥሉ መስማማቱ የልጁን ክስ ውድቅ ያደርገዋል።
አዛውንቱ ከፍቅረኛቸው ጋር ለ50 ዓመታት አብረው የቆዩ በመሆኑ፣ ሴቲቱ ንብረታቸውን ለመቀማት አታልላቸዋለች የሚል ማስረጃ እንደሌለም ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ ለአዛውንቱ ቢፈርድም፣ ልጃቸው የይግባኝ ጥያቄ በማቅረቡ ጋብቻቸው ለጊዜው መዘግየቱን ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቧል።
