banner

ለሰርጉ እየተዘጋጀ የነበረው ወጣት ቴዎድሮስ አዲሱ ሞሲሳ አሳዛኝ እረፍት

#FastMereja I ​የጋብቻ ስነ ስርዓቱን ለመፈጸም አንድ ወር ብቻ ቀርቶት የነበረው ወጣት ቴዎድሮስ አዲሱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
​
የነቀምቴ ከተማ ተወላጅ ነው። የመሠረታዊ ትምህርቱን በነቀምቴ ካቶሊክ ኪዳነ ምህረት ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በነቀምቴ ትምህርት ቤት አጠናቆ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል።

​በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት Ground Technician የአውሮፕላን ጥገና እና ደህንነት ቁጥጥር ላይ ሲሰራ ቆይቷል።
​
ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ካናዳ በማቅናት እዚያው በሙያው እያገለገለ ይገኝ ነበር። ​ቴዎድሮስ በወጣትነት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሲሆን፣ አስከሬኑ ዛሬ ወደ ትውልድ ከተማው ነቀምቴ እየሄደ መሆኑ ተገልጿል።

​ፈጣሪ ለነፍሱ ምህረትን ይስጥ፤ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። 💔

Leave a Comment