0
————————-
📅 የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መሪዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ አማኞች የሚሳተፉበት ለአንድ ወር የሚቆይ የጾም እና ጸሎት አዋጅ ይፋ አድርገዋል።
ጸሎቱ ከየካቲት 30 እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ አንድ ወር ይቆያል።ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እና ስለ ሀገር ሰላም የሚጸለይበት ሲሆን፤ የንስሐ፣ የምስጋና እና የምልጃ ጸሎቶችን ያካተተ ነው።
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ መሪዎች፣ አገልጋዮችና ምዕመናን በሙሉ በጋራ በጸሎት እንዲተጉ ጥሪ ቀርቧል።
#FastMereja #ማህበራዊ
