0
#Fastmereja I ዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር “የቡና ባህላችን ለሀገራዊ አንድነታችንና ለኢኮኖሚ እድገታችን” በሚል መሪ ቃል 2ኛውን የኢትዮጵያ የቡና ባህል ቀን ፌስቲቫል በዛሬዉ እለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት አክብሯል።
ይህ ፌስቲቫል ዝም ብሎ የቡና መጠጫ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን የሀገር ኩራት የሆነውን የቡና ባህላችንን በዓለም አቀፉ የቅርስ ተቋም (UNESCO) እንዲመዘገብ የሚደረግበት ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን የዋርካ ኮፊ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰአዳ ሙስጠፋ ገልፀዋል።
በዛሬዉ መርሀ-ግብር የአስራ አንዱም ክልሎች ውብ የቡና ባህል አልባሳት እና የቁሳቁስ አውደ-ርዕይ፣በእናቶቻችን እጅ የሚፈሉ ጣፋጭ ቡናዎችና የባህል የቡና ቁርሶች፣የስዕል ኤግዚቢሽን፣ የእደ ጥበብ ስራዎች ባዛርና ልዩ ልዩ ጌሞች እንዲሁም ሌሎች መርሀ-ግብሮች ተከናዉነዋል።
በፌስቲቫሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ዲፕሎማቶች፣በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤምባሲ አምባሳደሮች፣የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች እንዲሁም የቡና ላኪዎችና ተመራማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
#ኹነት




