banner

“አሁን ቢሆን ወንድሜ ሊተርፍ ይችል ነበር” ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

#FastMereja I ​የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ “ሚሻል ሁሴን ሾው” በተሰኘው የፖድካስት ፕሮግራም ላይ ቀርበው በልጅነታቸው በኩፍኝ በሽታ ስለሞተው ታናሽ ወንድማቸው አሳዛኝ ትዝታ አጋርተዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደገለጹት፣ በወቅቱ የነበረው የህክምና እጥረት ለወንድማቸው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል። “አሁን ባለው ቴክኖሎጂ ቢሆን ኖሮ ሊተርፍ ይችል ነበር” በማለት የሳይንስ እድገት ያለውን ፋይዳ ጠቁመዋል።

ዛሬ ላይ ክትባትና በቂ ህክምና ባለበት ዘመን ህፃናት አሁንም በኩፍኝ በሽታ መሞታቸው “ስህተት” እና ሊታረም የሚገባው ጉዳይ መሆኑን በቁጭት ገልጸዋል።

​ይህ የዶ/ር ቴዎድሮስ የግል ታሪክ፣ በአለም ዙሪያ ያሉ ህፃናት ሁሉ እኩል የህክምና አገልግሎትና የክትባት አቅርቦት እንዲያገኙ ለሚያደርጉት ተሟጋችነት ትልቅ መነሻ መሆኑን ያሳያል።

#ልዩ_ልዩ

Leave a Comment