banner

ኢራን በኩዌት ላይ 178 ባሊስቲክ ሚሳይሎች እና 384 ድሮኖችን አዝንባለች።

#FastMereja I የኢራን ወታደራዊ ጥቃት በኩዌት ላይ ከተሰነዘረበት ጊዜ ጀምሮ 178 የባሊስቲክ ሚሳይሎች እና 384 ድሮኖች ተለይተው መከሸፋቸውን የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ማክሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

​የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሳዑድ አል-አትዋን እንደገለጹት፣ ጥቃቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 27 የኩዌት ጦር አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። የቆሰሉት ወታደሮች ሁኔታ ቀላል ቢሆንም ሁለቱ አሁንም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል።

​የኩዌት ጦር ኃይሎች በከፍተኛ ንቃት ላይ እንደሚገኙና በየሰዓቱ የሚከሰቱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በቅርበትና በጥንቃቄ እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል።

Leave a Comment