banner

አዳማ ትራኦሬ በዌስትሃም የክብደት ማንሳት ልምምድ እንዳያደርግ ታገደ

​#FastMereja I የዌስትሃም ዩናይትድ ክንፍ ተጫዋች የሆነው አዳማ ትራኦሬ በክለቡ የክብደት ማንሳት ልምምድ እንዳይሰራ መታገዱን አሰልጣኝ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶ ገለጹ።

​በግዙፍ የሰውነት ቅርጹ የሚታወቀው ትራኦሬ፣ ከዚህ በላይ ጡንቻውን እንዲያጎለብት እንደማይፈለግ አሰልጣኙ በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል። ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶ ሲናገሩ፡ “ከጂም እንዲርቅ ነግሬዋለሁ። አሁን ላይ የተሸከመው ክብደት በቂ ነው፤ እሱ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ አይደለም” ብለዋል።

​እንደ አሰልጣኙ ገለጻ፣ ተጫዋቹ በጂም ውስጥ ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ ቀላል እንቅስቃሴዎችን ብቻ እንዲያደርግ ይፈቀድለታል። ከዚህ ውጪ ግን ማንኛውንም አይነት ክብደት የማንሳት ልምምድ እንዳያደርግ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቶታል።

​ይህ ውሳኔ የተላለፈው ተጫዋቹ በአሁኑ ወቅት ያለው የጡንቻ መጠን ለኳስ ተጫዋችነት ከበቂ በላይ በመሆኑና በሜዳ ላይ ያለውን ቅልጥፍና ለመጠበቅ ታስቦ እንደሆነ ተመልክቷል።

Leave a Comment