0
#FastMereja I የገጣሚ መላኩ ጌታቸው አዲስ የሥነ-ጽሑፍ ሥራ የሆነው “የህሊና ዜጎች” የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዘመን ሲኒማ በደመቀ ሥነ-ሥርዓት ተመርቋል።
በምረቃ መርሃ-ግብር ላይ ታዋቂ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች እና ደራሲያን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣የሚዲያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ገጣሚ መለኩ ጌታቸው ከዚህ ቀደም “የአርነት መንገድ” የተሰኘ የግጥም መጽሐፍ፣ “ባልና ሚስት” የተሰኘ ፊልም በድረሰት፣ እንዲሁም “ፈጣኖ ደራሹ ማኅበር” የተሰኘ የታሪክ መጽሐፍ በረዳት አዘጋጅነት ለንባብና ለተመልካች አቅርበዋል።
ይህ አዲሱ “የህሊና ዜጎች” መጽሐፍ 42 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ148 ገጽ ተሰንዶ በ400 ብር ለገበያ በቅቷል።




