#Fastmereja: በኢትዮጵያ የልደት ጉድለቶችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ ሮታሪ ኢትዮጵያ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ የወሊድ ጉድለቶች አሊያንስ እና ከሌሎች ቁልፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የልደት ጉድለቶችን መከላከል፣ እንክብካቤ እና ማካተት ላይ ያተኮረ የተሟጋችነት ዝግጅት በዛሬዉ አካሂዷል።
በአመት 41ሺህ የሚሆኑ ህፃናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር እንደሚወለዱ ተገልፆ ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ መከላከል በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን የሚያጠቃውን ስፒና ቢፊዳ (የአከርካሪ አጥንትና የነርቭ ዘንግ ክፍተት) እና ተያያዥነት ያለውን ሀይድሮሴፋለስ (በጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት) ችግሮችን በመከላከል ላይ ትኩረቱን መርሀ-ግብር ነዉ የተከናወነዉ።
ስፓይና ቢፊዳ (የነርቨ ዘንግ አፈጣጠር ) ችግሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር በአግባቡ አለመዘጋት/ክፍተት ነው፡፡
ሃይድሮሴፋለስ (የጭንቅላት ውስጥ ከመጠን በላይ የፈሳሽ ክምችት) ሲሆን ይህም የአዕምሮ ግፊት እንዲጨምርና የራስ ቅል ላይ መሰንጠቅን ሊያስከትል ይችላል።
ቅድመ መከላከል በችግሩ ለተጎዱ ቤተሰቦችና ግለሰቦች የህይወት ጥራትን ለማሻሻል ወሳኝ መፍትሄ መሆኑ ተገልጿል።
ዋናው የመከላከል ስትራቴጂ ጉባኤው ትኩረት ካደረገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ ምግብን በፎሊክ አሲድ ማበልፀግ ነው፡፡
ዋና ዋና ምግቦችን (እንደ ስንዴ ዱቄት፣ ዘይትና የምግብ ጨው) በፎሊክ አሲድ ማበልጸግ የነርቭ ዘንግ ክፍተትን በእጅጉ የሚቀንስ የተረጋገጠ ሳይንሳዊ ዘዴ ነው፡፡
ዝግጅቱ በነርቨ ቱቦ ጉድለቶች (ሃይድሮሴፋለስ እና ስፒና ቢፊዳን ጨምሮ) ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል።
ይህ ፕሮግራም ፖሊሲ አውጪዎችን፣ የጤና ባለሙያዎችን እና ተሟጋቾችን በመውለድ ችግር ላለባቸው ህጻናት የህይወት ጥራትን ለመከላከል እና ለማሻሻል ስልቶችን ለመወያየት አንድ ላይ የሚያሰባስብ እንደሆነ ነዉ የተገለፀዉ።




