0
#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን ጭማሪ ተከትሎ በሕዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
ቢሮው መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ ይውላል። ይህ ማሻሻያ የከተማ አውቶብስ፣ የሚኒባስ፣ የሚዲባስና የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ሁሉ የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል።
