banner

ዶክተር ኤርሚያስ በአሜሪካ በጾታዊ ጥቃት ወንጀል ተከሰሱ

​#FastMereja I ዋሽንግተን ዲሲ

​በሜሪላንድ ስቴት ሲልቨር ስፕሪንግ ውስጥ የሚሰሩት ዶክተር ኤርማያስ ሰማዬ፣ አንዲትን ታካሚ በቢሮአቸው ውስጥ ጾታዊ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፎክስ 5 ዘግበዋል።

​የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ዶክተር ኤርማያስ መጋቢት 10 ቀን (March 19) በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ በሦስት የጾታ ጥቃት እና በአምስት የትንኮሳ ወንጀል ክሶች ተመስርቶባቸዋል። ተጎጂዋ ግለሰብ ጥቃቱን ለፖሊስ ያመለከተችው በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ መሆኑ ታውቋል።

​የመጀመሪያው ጥቃት (የካቲት 11/Feb 19)፦ የጥርስ ንጽህና ባለሙያዋ ክፍሉን ለቅቃ እስክትወጣ በመጠበቅ፣ ዶክተሩ ጣታቸውን የታካሚዋ አፍ ውስጥ በማስገባት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት መፈጸማቸው ተገልጿል።

​ሁለተኛው ጥቃት (የካቲት 19/Feb 27)፦ ተጎጂዋ ለጥንቃቄ ጓደኛዋን ይዛ ብትመጣም፣ ዶክተሩ ጓደኛዋን ከክፍል ውጭ እንድትጠብቅ በማሳመን ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸው ተመልክቷል።

​ፖሊስ እንደገለጸው፣ ዶክተር ኤርማያስ ከተጎጂዋ ጋር በስልክ ባደረጉትና መርማሪዎች በድብቅ ባዳመጡት ንግግር ድርጊቱን መፈጸማቸውን አምነዋል።

መርማሪዎች ባደረጉት ማጣራት እ.ኤ.አ በ2018 በተመሳሳይ ድርጊት በዶክተሩ ላይ ጥቆማ ቀርቦ እንደነበር ደርሰውበታል። በወቅቱ በወንጀል ባይከሰሱም፣ የህክምና ፈቃዳቸው ለተወሰነ ጊዜ ታግዶ በክትትል ስር እንዲቆዩ ተደርጎ እንደነበር ተጠቁሟል።

​ፖሊስ ሌሎች ተጎጂዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ግምት ስላለው፣ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።
​
መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም

Leave a Comment