0
#FastMereja I በሸካ ዞን ማሻ በአምቡላንስ እጥረት ምክንያት አንዲት ምጥ ላይ ያለች እናት በሞተር ሳይክል ተጭና ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጣ ከተጓጓዘች በኋላ፣ በማሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላት አስቸኳይ ቀዶ ህክምና የእናትና የልጇ ሕይወት ተረፈ። ድርጊቱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
ነፍሰ ጡር እናቷ ከጫጎ ጤና ጣቢያ ወደ ማሻ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተሻለ ሕክምና ሪፈር ተባለች።
በወቅቱ የአምቡላንስ አገልግሎት ባለመገኘቱ፣ እናቷን እጅግ አደገኛ በሆነ ሁኔታ በሞተር ሳይክል ጭኖ ወደ ሆስፒታል ለማጓጓዝ ተገዷል።
ለአምቡላንስ አገልግሎት መቋረጥ በምክንያትነት የቀረበው “የናፍጣ እጥረት” እንደሆነ ተገልጿል።
እናቷ ሆስፒታል ከደረሰች በኋላ በባለሙያዎች ብርቱ ርብርብ በቀዶ ሕክምና በሰላም ተገላግላለች። በአሁኑ ወቅት እናትና ልጇ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
