banner

ሲኖትራክ በአዲስ አበባ ባቡር ገጨ

​#FastMereja I አዲስ አበባ

​በየካ ክፍለ ከተማ ሠዓሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ዛሬ ረፋድ ላይ አንድ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከቀላል ባቡር ጋር በመጋጨቱ በሁለት ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው ከቀኑ 5፡55 ሰዓት አካባቢ ሲኖትራኩ ከላምበረት ወደ ጃክሮስ ሲጓዝ ከነበረ ባቡር ጋር በመጋጨቱ ነው።

​የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ንብረት የሆነ የሰሌዳ ቁጥር 5-82D11-2 ሲኖትራክ እና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ቁጥር 111 ናቸው።

​አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን በመቆጣጠር እና የመንገዱን አቀማመጥ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።




Leave a Comment