banner

የ2018 የፋሲካ ኤክስፖ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታጅቦ ተከፈተ!

#FastMereja I አዋሽ ባንክ ከታሚሶል ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና የ2018 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት ያደረገው “የአዋሽ ብር ፕሮ፣ ፋሲካ ኤክስፖ” የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል።

ባንኩ የታይትል ስፖንሰር በመሆን ያዘጋጀው ይህ የንግድ ትርኢትና ባዛር ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በርካታ ሸማቾችና ነጋዴዎችን በአንድ ስፍራ በማገናኘት የበዓል ገበያውን ያቀላጥፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

በዘንድሮው ኤክስፖ አዋሽ ባንክ “አዋሽ ኢ‐ቲኬቲንግ” የተሰኘ አዲስ የዲጂታል መተግበሪያን በይፋ አስተዋውቋል።

ባንኩ የዲጂታል ግብይትን ለማበረታታትና የደንበኞቹን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በአዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ መተግበሪያ በመጠቀም ቲኬት ቆርጦ ለሚያሸንፍ እድለኛ የቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል የኤሌክትሪክ መኪና ባለእድል እንደሚሆንም ነዉ የተገለፀዉ።

በ“አዋሽ ብር ፕሮ“ በኩል ግብይት ለሚፈጽሙ ሸማቾች የ5 በመቶ ተመላሽ (Cashback) ተጠቃሚ እንደሚሆኑም በመክፈቻዉ ተገልጿል።

በኤክስፖው ወቅት ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንደሚኖር በመገመቱ፣ ባንኩ በኤግዚቢሽን ማዕከሉ ውስጥ የተሟላ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥበትን አሠራር ዘርግቷል ይህም ሸማቾችና ነጋዴዎች ያለምንም እንግልት የፋይናንስ ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟሉ ያስችላቸዋል፡፡

መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም





Leave a Comment