0
#FastMereja I በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባንቢስ አካባቢ የሚገኘው ዲሊኦፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል፣ የሽንት ቤት ፍሳሽን ወደ ወንዝ በመልቀቅ በፈጠረው ከፍተኛ የአካባቢ ብክለት ምክንያት የ600 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተጣለበት። ሆቴሉ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጥፋት ተቀጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ ድርጊቱን በመደጋገሙ ምክንያት የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቅጣቱን ወደ እጥፍ ለማሳደግ መገደዱን አስታውቋል።
ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የተካሄደውን የክትትል ውጤት ተከትሎ፣ የብክለቱ መንስኤ የሆኑት የሆቴሉ መጸዳጃ ቤቶች ችግሩ ተወግዶ ጤናማ የአወጋገድ ሥርዓት እስኪዘረጋ ድረስ እንዲታሸጉ ተደርጓል። ባለስልጣኑ የከተማዋን ወንዞችና ተፋሰሶች ደህንነት ለመጠበቅ በብክለት ፈጣሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፣ ህብረተሰቡ መሰል የደንብ መተላለፎችን ሲመለከት በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
