banner

የከተማዋን ገጽታ ለውጥ የሚዘክር መጽሐፍ ተመረቀ

#FastMereja I የአዲስ አበባን የከተማ ትራንስፎርሜሽን እና የመልሶ ማልማት ጉዞ የሚተርከው “THE REMAKING OF ADDIS ABABA/አዲስ አበባን እንደ አዲስ” የተሰኘ መጽሐፍ ዛሬ ተመርቋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በከንቲባ አዳነች አቤቤ በተመረቀው በዚህ መጽሐፍ ላይ የውጭ ሀገር ምሁራንና ጸሐፊዎች የከተማዋን የለውጥ አሻራ በዝርዝር አስፍረዋል።

መጽሐፉ በእንግሊዛዊው ፕሮፌሰር ሲሞን ሊ፣ በዶ/ር ክሌመንት ካቱሉሺ እና በትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ሂርጶ ቁምቢ መሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ጸሐፊዎቹ ስራውን ያከናወኑት በራሳቸው ተነሳሽነትና ወጪ መሆኑ ተገልጿል። በምረቃው ወቅት እንደተጠቀሰው፣ መጽሐፉ የአስተዳደሩን ቃል በተግባር የመለወጥ ሂደት፣ የህዝብ ተሳትፎን እና የአዲስ አበባን ወቅታዊ ገጽታ ለትውልድ በሚተላለፍ መልኩ የሰነደ ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መጽሐፉ ጠንካራ እሳቤዎች ወደ ተጨባጭ ስኬት መቀየራቸውን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፣ ለከተማዋ እድገት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ እውቅና ሰጥተዋል። ይህ የለውጥ ጉዞ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎቿን ኩራት የጨመረ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ በቀጣይም የከተማዋን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል።





Leave a Comment