#FastMereja I የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን የቪዛ አመልካቾች ላይ ጥሎት የነበረውን ጥብቅ ገደብ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ተከትሎ፣ መደበኛው የ Schengen ቪዛ አሰጣጥ ሂደት በድጋሚ ስራ መጀመሩ ተገለጠ። ህብረቱ በቪዛ ህጉ አንቀፅ 25ሀ (Article 25a) ስር ደንግጎት የነበረውን ጊዜያዊ ገደብ ያነሳው ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ለቪዛ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ እና ባለብዙ መግቢያ (Multiple-entry) ቪዛ አሰጣጥ ደንቦች ወደ ቀድሞው መደበኛ አሰራር እንዲመለሱ ተደርጓል።
ይህ ውሳኔ ባለፉት ወራት በአመልካቾች ላይ ተከስቶ የነበረውን ረጅም የጥበቃ ጊዜ እና የሰነድ ማጣራት ውክቢያ በከፍተኛ ሁኔታ ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል። የአውሮፓ ህብረት ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በስደተኞች አመለስለስ ዙሪያ በነበረው አለመግባባት ሳቢያ የቪዛ አሰጣጥ ሂደቱን አጥብቆት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ የታየው የመንግስት ትብብር ለገደቡ መነሳት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ውሳኔው በተለይም ለንግድ፣ ለትምህርትና ለህክምና ወደ አውሮፓ መጓዝ ለሚፈልጉ ዜጎች ትልቅ እፎይታን የፈጠረ ሲሆን፣ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም አመልካች በተለመደውና ቀልጣፋ በሆነው የስራ አሰራር መሰረት ማመልከት እንደሚችል የአምባሳደሮች መግለጫ ያመላክታል።
