banner

አርሰናል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የታሪክ ሪኮርድ ሰባበረ!

​#FastMereja I መድፈኞቹ የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቃቸውን በታላቅ ድል ካበቁ ማግስት፣ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛውን የገቢ መጠን በመሰብሰብ አዲስ የፋይናንስ ታሪክ አስመዝግበዋል። ክለቡ በዚህ የውድድር ዘመን 760 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ በሃንጋሪ ቡዳፔስት ከፓሪስ ሳንዠርሜን ጋር በሚያደርገው የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ድል የሚቀናው ከሆነ አጠቃላይ ገቢው ወደ 770 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍ ይላል።

​ይህ አስገራሚ አሃዝ ማንቸስተር ሲቲ ቀደም ሲል አስመዝግቦት የነበረውን የ715 ሚሊዮን ፓውንድ የፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ የገቢ ሪኮርድ በይፋ የሰበረ ነው። ዘ ታይምስ ጋዜጣ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፣ አርሰናል ይህንን ግዙፍ የፋይናንስ አቅም ሊገነባ የቻለው ከከፍተኛ የቴሌቪዥን ስርጭት መብት ሽያጭ፣ ከስታዲየም መግቢያ ትኬት እና ከዋና ዋና ስፖንሰሮቹ እንደ ኤሚሬትስ እና አዲዳስ ከሚያገኛቸው የፋይናንስ ቦነሶች የተነሳ ነው።

Leave a Comment