banner

“የአዶ ትዝታዎች” መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመረቀ

​#FastMereja I “የአዶ ትዝታዎች” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመርቋል። መጽሐፉ በፕሮፌሰር ታሪክ ወልደሚካኤል እና በአቶ ሙሉጌታ ወልደሚካኤል በጋራ የተሰናዳ ሲሆን፣ የአያታቸውን ታሪክ ዋቢ በማድረግ ከጉራጌ ማህበረሰብ ምድር ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የተደረጉ ታሪካዊና ትውልድ ተሻጋሪ የህይወት ጉዞዎችን በስፋት የሚዳስስ ነው።

​ዛሬ ለምረቃ የበቃው ይህ መጽሐፍ፣ በተለይም ውድ አያት ኑሮን ለማሸነፍ የከፈሉትን ከፍተኛ ተጋድሎና ያጋጠሟቸውን አስገራሚ ክስተቶች በሳቅና በትዝታ ታጅቦ በሚያስነብብ መልኩ እንደተከተበ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ የክቡር አባታችን የአቶ ወልደሚካኤል አንዳግቤ እና የውድ እናታችን የወ/ሮ አስካለ ኃብተማርያም ከጉራጌ ዞን እስከ አዲስ አበባ የዘለቀውን አስደናቂ የህይወት ጉዞ፣ ህይወትን ለመለወጥና ቤተሰብን ለመገንባት ያደረጉትን ተጋድሎ፣ ያፈሩትን ሀብትና ያጋጠሟቸውን ውጣ ውረዶች በግልጽ ያሳያል።

​ፈጣሪ የሰጠንን ችሎታና ማስተዋል ለበጎ ነገር ማዋል እንደምንችል የምንማርበት፣ ከየትኛውም ከባድ ውድቀት መነሳት እንደሚቻል የሚያሳይና የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያጸና የታሪክ መዝገብ ነው የተባለው የዚህ መጽሐፍ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወዳጅ ዘመዶችና የመጽሐፍ አፍቃሪያን በተገኙበት በስኬት ተጠናቋል።





Leave a Comment