0
#FastMereja I በትግራይ ክልል ተምቤን ዓቢይ ዓዲ ከተማ የሚገኙ ልጃገረዶች ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የኣሸንዳ በዓልን በታላቅ ድምቀት በማከበር ላይ ይገኛሉ።
የከተማዋ ልጃገረዶች እና ታዳጊዎች በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በመገኘት “ማርያምዋይ ፀሓየ መፂአያ ኮ ዛ መፅብዓየ” በሚሉ ህያው የጸሎትና የምስጋና ዜማዎችና ግጥሞች ታጅበው የበዓሉን ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል። ታዳሚዎቹ የነበሩበትን የነሐሴ ጾም ፍጻሜና የፍልሰታ ማርያም በዓልን አስመልክቶ የቀረበው ይህ ምስጋና፣ የዓቢይ ዓዲ ከተማ ነዋሪዎችንና እንግዶችን ቀልብ ስቧል።




