banner

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የግማሽ ማራቶን የዓለም ሪኮርድን በአስደናቂ ሁኔታ ሰበረ

#FastMereja I ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ዮሚፍ ቀጄልቻ በቡኤኖስ አሬስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር 56 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ሪኮርድ አስመዝግቧል።

በአርጀንቲና ዋና ከተማ ቡኤኖስ አሬስ ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ዮሚፍ፣ ከዚህ ቀደም በኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ የነበረውን የ57 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ሪኮርድ በ29 ሰከንዶች ማሻሻል ችሏል። በዚህም ውጤት ዮሚፍ በታሪክ የመጀመሪያው የግማሽ ማራቶን ርቀትን ከ57 ደቂቃ በታች በመግባት ያጠናቀቀ አትሌት በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

ይህ አስደናቂ የስፖርት ስኬት ዮሚፍ ቀጄልቻ በዘመናዊው የረጅም ርቀት ሩጫ ላይ እያሳየ ያለውን የበላይነት ያረጋገጠበት ሌላው ክስተት ነው። አትሌቱ ባለፈው ሚያዝያ ወር በለንደን ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋዊ የውድድር መስመር ማራቶንን በ1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በመጨረስ ከሁለት ሰዓት በታች በይፋ ከሮጡ ጥቂት አትሌቶች አንዱ መሆኑ ይታወሳል።

Leave a Comment