0
#FastMereja I በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ፅምብላ ወረዳ ዓዲ ገብሩ ከተማ እና አካባቢዋ ከ13 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር የሚቀርፍ፣ በ35 ሚልዮን ብር በጀት በሶላር ኤነርጂ የሚሰራ የውሃ ፕሮጀክት ተገንብቶ ለምረቃ የበቃ ሲሆን ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ይህ በዓዲ ገብሩ ከተማ እና በህንፀት ጣቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የውሃ ፕሮጀክት በሉትራን ዓለም ለኸ ፌደሬሽን (LWF)፣ 3R እና ወርልድ ቪዥን በተሰኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከትግራይ ክልል ውሃ እና ኤነርጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የተገነባ ነው። ፕሮጀክቱ በሰከንድ 9 ሊትር ውሃ የማምረት አቅም ያለው በመሆኑ በቆሸሸ ውሃ ምክንያት ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች ሲጋለጡ እና ንጹህ ውሃ ፍለጋ ረጅም ኪሎ ሜትሮችን ሲጓዙ ለነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ዘላቂ መፍትሔ ይዞ መጥቷል።



