0
#FastMereja I በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በሀድያ ዞን ግቤ ወረዳ የተገኘው የሊች ጎጎ ትምህርት ቤት ተማሪ ሮቤል ጌታቸው ገብሬ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከቀረቡበት 600 ጥያቄዎች ውስጥ 590 ያህሉን በትክክል በመመለስ አስደናቂ የስኬት ታሪክ አስመዝግቧል።
ይህ የተመዘገበው የላቀ ውጤት በዘመኑ የፈተና ታሪክ ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛው ከፍተኛ ውጤት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፣ የተማሪውን ጠንካራ የጥናት ባህልና በትምህርቱ ላይ የነበረውን ከፍተኛ ትጋት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። የተማሪ ሮቤል ጌታቸው ስኬት ለተማረበት ሊች ጎጎ ትምህርት ቤት፣ ለዞኑ እንዲሁም ለመላው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትልቅ ኩራትና ለቀጣይ ተፈታኞችም አርአያ የሚሆን አዎንታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተጠቅሷል።
