banner

የላቁ የቴክኖሎጂ ስልጠናዎች በምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል ሊሰጡ ነው!

​
#FastMereja I «ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» አገራዊ ራዕይን ለማገዝ እና አዲስ አበባን «ስማርት ሲቲ» ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚያፋጥን የጋራ ትብብር ስምምነት ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ይፋ ሆኗል።

ስምምነቱ በሮቴክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል መካከል የተከናወነ ሲሆን፣ በኮምፒውተር ዘርፍ ለመሰልጠን ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች በ3 ወራት ውስጥ አሰልጥኖ ወደ ሥራ ዓለም ለማሰማራት ያለመ ነው።

​ይህ የፈጠራ እና የክህሎት መርሃ-ግብር እንደ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፣ የላቁ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች፣ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ፣ የሃርድዌር እና የሶፍትዌር ጥገናን ያካተቱ 7 ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ያተኩራል። ስልጠናው በቀጥታ ወደ ተግባራዊ የሥራና የቢዝነስ ዓለም የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል።

​ይህ ጅምር በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚስተዋሉትን የክህሎት ክፍተቶች በመሙላት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትና አገሪቱ ለያዘችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግብ ትልቅ በር ከፋች እንደሚሆን ታውቋል።





Leave a Comment