banner

ኤርትራ “ኢትዮጵያ ራስን በመከላከል ስም ልትወረኝ ነው” ስትል ከሰሰች

#FastMereja I የኤርትራ መንግሥት ፕሬስ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት “ሉዓላዊ የባህር በር ማግኘት” እና የባህርኃይል አቅምን ለመገንባት በሚል ሽፋን በኤርትራ ላይ የጥቃት ጦርነት ለመክፈት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው አለ። የኤርትራ መንግሥት ቃለ አቀባይ የማነ ገብረመስቀል ከሰዓታት በፊት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በኤርትራ ላይ የሐሰት ውንጀላዎችን በመሰንዘር አጀንዳቸውን በ”ራስን የመከላከል” ስም ለመሸፈን እየሞከሩ ነው ብለዋል።

​በመግለጫው እንደሰፈረው፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የተሰሙ ከፍተኛ የሰራዊት ጄኔራሎች አስተያየቶች የኢትዮጵያን እውነተኛ አላማ የሚያሳዩ ናቸው። በተለይም አንድ ከፍተኛ ጄኔራል ለአገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃል “ዘመቻውን ስንጀምር ትግራይ ላይ አንቆምም… ዋናው አላማችን ባንዲራችንን ቀይ ባህር ላይ ማቆም ነው” ማለታቸው አሳሳቢ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት አመልክቷል። እንዲሁም “መቀሌ ማቆሚያ አይደለችም፣ የመጨረሻ መድረሻችን አሰብ ነው” የሚሉ ንግግሮች የኢትዮጵያን እቅድ ግልጽ የሚያደርጉ እንደሆኑ ገልጿል።

​የኢትዮጵያ መንግሥት ሆን ብሎ ጦርነቱን በራስን መከላከል ስም ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ቀባይነት የሌለው እና ክልላዊ ጸጥታን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል የኤርትራው ቃለ አቀባይ ማነ ገብረመስቀል በመግለጫቸው ገልጿል።

10 comments

Mihert Ab Dejene October 7, 2026 - 5:42 pm

ነውራም ባአለጌ

Reply
Daniel Kasaye October 7, 2026 - 5:42 pm

በጣም ነው እንዴ የፈራችው

Reply
Exact Way October 7, 2026 - 5:43 pm

የአባቶቻችን ደም እንመልሳለን

Reply
Dawit Lemma October 7, 2026 - 5:43 pm

ይህች አደገኛ ፖለቲካ ነሽ

Reply
Wesenu Wedajo October 7, 2026 - 5:44 pm

የኛን ለኛ!

Reply
Tsegaye Gasare October 7, 2026 - 5:44 pm

ዋናው ነገር ማወቅህ ነው

Reply
Legese Belete October 7, 2026 - 5:44 pm

ሌላ እልቂት አይ አፍሪካ

Reply
Meskerem Ute October 7, 2026 - 5:45 pm

ዉሸታሞች ናቸው😭

Reply
ማዕዶት ቤተክርስቲያን October 7, 2026 - 5:45 pm

ጥምዶ ያድንሽ በሏት

Reply
Woin Woin October 7, 2026 - 5:45 pm

2013 ከገቡ ላይ ከትግራይ ከገቡ ቆዩ እኮ አሁን ነው ትዝ የሚላችሁ

Reply

Leave a Comment