0
አሪፍፔ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ማህበረሰብ እና ከሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ማህበር ጋር የዲጂታል ትብብር ስምምነት ተፈራረመ
#FastMereja I አሪፍፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አ.ማ. ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበረሰብ እና ከሀዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ጋር የጋራ ትብብር ስምምነት ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም. ተፈራርሟል።
አሪፍፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እና ሀዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ዛሬ በአሪፍፔይ ዋና መስሪያ ቤት ባካሄዱት የፊርማ ስነ-ስርዓት፣ የእግር ኳስ ደጋፊዎችን ምዝገባ በዲጂታል መንገድ ማከናወንና ማቀላጠፍ። ከስፖርቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ የተለያዩ ምርቶችና ቁሳቁሶች ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ አማራጮች እንዲካሄድ ማድረግ። ደጋፊዎች በቀላሉ ተመዝግበው አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን የዲጂታል ክፍያ መፍትሄዎችን ማቅረብ ያካተት ነው።
ይህ ትብብር በኢትዮጵያ ውስጥ የእግር ኳስ ደጋፊዎችን ማህበረሰብ ወደ ዲጂታል አሰራር ለማሸጋገር እና የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።




