#Fastmereja:-19ኛው ዓለም አቀፍ የአከርካሪ ቀን “የአከርካሪ ጤና ለዕድሜ ልክ” (Spine Health for Life) በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የካይሮፕራክቲክ (Chiropractic) የአከርካሪ ሕክምና አገልግሎት ሰጪ በሆነው ፈርስት ስፓይን ክሊኒክ (First Spine Clinic) አዘጋጅነት በተለያዩ ንቅናቄዎች ተከብሯል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የክሊኒኩ መስራችና ባለቤት ዶ/ር ሰላም አክሊሉን ጨምሮ የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት በዳዳ፣ በርካታ የጤና ባለሙያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳታፊ ሆነዋል።
በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት በዳዳ እንደገለፁት፤ አከርካሪ የሰውነት መሰረት፣ ለነርቭ ስርዓት መተላለፊያና ጠባቂ በመሆኑ እንክብካቤው ለዕለት ተዕለት ህይወት ቁልፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ ትዕግስት አክለውም የዘንድሮው መሪ ቃል አከርካሪያችንን ህመም ወይም ጉዳት እስኪደርስበት ሳንጠብቅ በዕድሜ ልክ ኑሯችን ልንንከባከበው እንደሚገባ የሚያሳስብ መሆኑን አስረድተዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 1 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአከርካሪ ህመም እና አካል ጉዳት እንደሚሰቃዩ የተገለፀ ሲሆን፣ የጀርባ ህመም ዋነኛው የአካል ጉዳት መንስኤና በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ከሚያመጡ የጤና ችግሮች መካከል አንዱ መሆኑ ተመላክቷል።
በሀገራችንም ቢሮ ውስጥ ረጅም ሰዓት ተቀምጠው የሚሰሩ፣ የዕለት ተዕለት የጉልበት ሥራ የሚያከናውኑ፣ ውሃና ማገዶ የሚሸከሙ እንዲሁም የግንባታ ሠራተኞች ለአደገኛ የአከርካሪ ጭነት የተጋለጡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይም በገጠር አካባቢዎች ስለ አከርካሪ አጥንት አጠባበቅ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ ትኩረት እንደሚሻ ተጠቅሷል።
በዶክተር ሰላም አክሊሉ የተቋቋመው ፈርስት ስፓይን ክሊኒክ ላለፉት 25 ዓመታት ከቀዶ ጥገና ነፃ በሆነ የካይሮፕራክቲክ ሕክምና አገልግሎት በመስጠትና “ቀጥ ይበሉ” በተሰኘው ዘመቻው የኅብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ግንባር ቀደም ሚና ሲጫወት መቆየቱ በዝግጅቱ ላይ ተብራርቷል።





1 comment
የቱ አከርካሪ 🤔🤔