0
#FastMereja I በኢትዮጵያ ተወልዳ በዴንቨር ያደገችው የ29 ዓመቷ ዴሞክራቲክ ሶሻሊስት መላት ኪሮስ፣ በኮሎራዶ አንደኛ ምርጫ ክልል በተካሄደው የ2026 አሜሪካ አጋማሽ ምርጫ አሸናፊ በመሆን የኮንግረስ አባልነት ወንበርን ተቀናጅታለች። ይህ ውጤት ሜላት ከስቴቱ ወደ አሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የተመረጠች የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት እና የዚ (Gen Z) ትውልድ ተወካይ ያደርጋታል።
ሜላት ኪሮስ ለዚህ ታሪካዊ ውጤት ለመብቃት በቅድመ ምርጫው (Primary) ለ30 ዓመታት ወንበሩን ይዘው የቆዩትንዴሞክራቷን ዲያና ዲጌትን ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን፣ በዋናው ምርጫም የሪፐብሊካን እና የግል ተፎካካሪዎቿን በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ አሸንፋለች።
በምርጫ ቅስቀሳዋ ወቅት የሁሉንም ዜጎች የጤና ዋስትና (Medicare for All)፣ ተመጣጣኝ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት፣ የኮርፖሬሽኖችን የገንዘብ ተፅዕኖ ከፖለቲካ ማስወገድ እና የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎችን በዋናነት አንግባ ስትታገል ቆይታለች። እንደ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባ፣ የኮሎራዶ የመጀመሪያው የምርጫ ክልል በዴሞክራቶች ከፍተኛ ድጋፍ የሚታወቅ በመሆኑ የዚህ ምርጫ ውጤት የሜላት ኪሮስን የኮንግረስ ጉዞ በይፋ አረጋግጧል።
